ኢንሰትራክተር በአምላክ ተሰማ የአፍሪካን ዋንጫ በዋና ዳኝነት እንዲመሩ ተመረጡ

ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ በአምላክ ተሰማ ጋቦን ለምታስተናገደው የ2017ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ በዋና ዳኝነት እንዲመሩ ተመረጡ።
የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) በ31ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ 17 በዋና እና 21 በረዳት ዳኝነት የሚመሩ ዳኞችን ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል።
ከ17ቱ ዋና ዳኞች መካከል ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ በአምላክ ተሰማ አንዱ ሆነው ተመርጠዋል።
በአምላክ ተሰማ ኢካቶሪያል ጊኒ ያስተናገደችውን የ2015 የአፍሪካ ዋንጫ ጨምሮ በአህጉረዊ ውድድሮች በርካታ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን በመዳኘት ልምድ ያላቸው ዳኛ መሆናቸው ይታወቃል።
ለ2017ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ በዳኝነት የተመረጡት ከ17 አገራት ሲሆን፥ ኢትዮጵያን ጨምሮ ግብፅ፣ ቱኒዚያ፣ ዛምቢያ፣ ጋንምቢያ፣ አልጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካና ጋቦን ይገኙበታል።
ካሜሮን፣ ቦትስዋና፣ ማሊ፣ ሲሸልስ፣ ማዳጋስካር፣ ሞሮኮ፣ ሞሪታኒያ፣ ሴኔጋልና አይቮሪኮስት እያንዳንዳቸው ዳኞች ያስመረጡ አገራት ናቸው።
ኢትዮጵያዊቷ ኢንተርናሽናል ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ ካሜሮን እያስተናገደችው ባለው 10ኛው የሴቶች አፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ በዋና ዳኝነት እየመራች መሆኑ ይታወቃል።( ኢዜአ)
 
 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

shares